የፍቺ ውሳኔ የጋብቻ ውልን ቀሪ ያደርጋል ወይስ አያደርግም?

Authors

  • Dr. Dejene Girma Ethiopian Civil Service University

Abstract

በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው ሁኔታ ህጋዊ ጋብቻ ሁለት ተቃራኒ ፆታ ባላቸው ሰዎች መካከል ሊፈፀም የሚችል ግንኙነት ወይም ድርጊት
መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡1 ይህ ግኙነት በፅሁፍ ውል መመስረት ያለበት እና በአራት ምስክሮች ማለትም ሁለት ከባል እና ሁለት ከሚስት
በኩል መረጋገጥ ያለበት ውል እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡2 በዚህ ውል መሰረት ተጋቢዎች የጋብቻ/የትዳር ግንኙነት በመካከላቸው ሲመሰርቱ
ቀሪውን የህይወት ዘመናቸውን አብሮ በፍቅር፣ በመከባበር፣ መተጋጋዝ፣ እና በመረዳዳት ለማሳልለፍ በመወሰን ነው፡፡3 በዚሁ መሰረት
ሰዎች ወደ ጋብቻ ይጋባሉ፤ ትዳር ይመሰርታሉ፣ ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር እስከ መጨረሻም ይኖራሉ፡፡ ነገር ግን በተለየዩ ምክንያቶች
የታሰበው ሳይሆን ወደ ጋብቻ ከሚገቡ ሰዎች መካክ የተወሰኑቱ ጋብቻቸው ሊፈርስ ይችላል፡፡ ከእነዚህ ምክንያቶች መካከከል አንዱ ፍቺ
ነው፡፡ ፍቺ በፍርድ ቤት የሚሰጥ ውሳኔ ሲሆን ይህ ውሳኔ በተጋቢዎች መካከል የነበረው ግንኙነት የሚያቋርጥ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ
በርካታ ነጥቦች ሊነሱ ቢችሉም የዚህ ፅሁፍ ትኩረት አንዱ ላይ ብቻ ሲሆን እርሱም ሰዎች የፅሁፍ የጋብቻ ውል ፈፅሞ ከተጋቡ በኋላ
ጋብቻቸው በፍ/ቤት ቢፈርስ የፍቺ ውሳኔ በጋብቻ ውል ላይ ያለው ውጤት ምንድን ነው? የሚል ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ መንስዔ የሆነ አንድ
የፍ/ቤት ውሳኔ ሲሆን የነገሩ አመጣጥ በአጭሩ እንደሚከተለው ነው፡፡

Author Biography

Dr. Dejene Girma, Ethiopian Civil Service University

Assitant Professor, School of Law, Ethiopian Civil Service University 

Additional Files

Published

2024-08-28

Issue

Section

Ethiopian Journal of Legal Studies